ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ
መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው […]