በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ
    • ታሪክ
    • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
    • ካህናት
  • አገልግሎት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ህጻናት እና አዳጊዎች
  • ትምህርተ ሃይማኖት
  • ይለግሱ
  • ያግኙን
  • Menu Menu
Blog - Latest News

መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)

 
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

አምላኩሰ ለአዳም ለዕረፍት ሰንበተ ሠርዓ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ ወይቤሎሙ ኢየሱስ አነኒ እገብር አንትሙኒ እመኑ ለግብርየ ወይቤሎሙ አነ ውእቱ እግዚኦ ለሰንበት እግዚኦ ውእቱ ለሰንበት ወልድ ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውህ ሊተ እኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር እስበክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ

ትርጉም: “የአዳም ፈጣሪ ለዕረፍት ሰንበትን ሠራ፤ አይሁድም በማን ሥልጣን ይህን ታደርጋለህ አሉት፤ እርሱም እኔ እሠራለሁ እናንተም ሥራዬን እመኑ አላቸው፡፡ የሰንበት ጌታው እኔ ነኝ፤ የሰንበት ጌታው/የአብ/ አንድያ ልጁ ነው፡፡ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር እል ዘንድ ፣ ነፃነትን እሰብክ ዘንድ ተሰጥቶኛል ፣ የዕውራንን ዓይን አበራ ዘንድ አባቴ ልኮኛል አላቸው፡፡” ማለት ነው፡፡

 

ምንባባት/መልዕክታት/

ገላ. 5÷1-ፍጻሜ ምዕ.እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡ እነሆ÷እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ “ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡”
ያዕ.5÷14- ፍጻሜ ምዕ.ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቅቡት፡፡
የሐዋ.3÷1-11 ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፡፡ ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁል ጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር፡፡
ምስባክ

መዝ.40÷3 “እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢ /ቤ/ሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዝኦ ተሣሃለኒ
ትርጉም፦ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል፡፡

ወንጌል
ዮሐ. 5÷1-24 ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት፡፡
                 የዐብይ ጾም ሥርዓት ለማዳመጥ ይህንን ሊንክ ይጫኑ -ቆይታ ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ጋር

 

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg 0 0 tc https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg tc2014-03-15 10:02:012014-03-15 10:02:01መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)
Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የእለተ ሰንበት ቅዳሴ ና ጸሎት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት ከስቶክሆልም ቅድስት ሥላሴ መንበረ ጸባኦት
  • ካህናት
  • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
  • የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ የንግሥ በዓል
  • የአጥቢያው የመተዳደርያ ደንብ ጸድቆ በሥራ ላይ ዋለ
  • ቀዳሚት ሥዑር
  • ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
  • ሆሣዕና
  • የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ
  • +++ የበገና እና የሥነ ጽሑፍ ምሽት +++

በፌስቡክ ያግኙን

© Stockholm Menbere Tsebaot Holy Trinity Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: አውደ ወራዙት (ወጣትነት በቤተክርስቲያን) Link to: አውደ ወራዙት (ወጣትነት በቤተክርስቲያን) አውደ ወራዙት (ወጣትነት በቤተክርስቲያን) Link to: ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ Link to: ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top