በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ
    • ታሪክ
    • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
    • ካህናት
  • አገልግሎት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ህጻናት እና አዳጊዎች
  • ትምህርተ ሃይማኖት
  • ይለግሱ
  • ያግኙን
  • Menu Menu
Blog - Latest News

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ምርጫ አካሄደ

pic-1ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ እና ሥራ አስኪያጁ መጋቤ አእላፍ ተወልደ ገብሩ እንዲሁም የአጥቢያው ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በተገኙበት የካቲት 02 ቀን 2006 ዓ.ም. በ S:t Jacobs Kyrka, Stockholm, Sweden ባደረገው አጠቃላይ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ ሕግና በሀገሩ የቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት:- መላከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ ካሳዬ አለሙ፣ ዲ/ን ተሻለ ቢያዝን፣ ዲ/ን ኪሮስ አብርሃ፣ ታሪኩ ተመስገን፣ ይሁን ድሌ፣ በላይነሽ ገዝሄ፣ ጸደይ ሀጎስ፣ ታጠቅ ፍቃዱ እና ተስፋየ ገ/ማርያም የአጥቢያው ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ሆነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ መርጦ ሰይሟል።

የአዲሱ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ በጠቅላላ ጉባኤው በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት በደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ አለሙ ሰብሳቢነት በቃለ አዋዲ ደንብ እየተመራ:-

 

  1. የአጥቢያው አገልጋይ ካህናትና ምእመናን የቤተክርቲያኗን ሕግ፣ ሥርዐት እና ቀኖና ጠብቀው እንዲያገለግሉና እንዲገለገሉ እንዲያደርግ፣
  2. የተዘጋውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሕግ አስከፍቶ የተለመደውን መንፈሳዊ አገልግሎት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል፣
  3. የቃለ ዓዋዲን ደንብ ከሀገሩ የሃይማኖት ተቋማት መመሪያ ጋር በማጣጣም የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀትና ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቦ በማስጸደቅ በሥራ ላይ እንዲያውል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል። 

pic-1የጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በከፊል

ብፁዕነታቸው አያይዘውም ለቀድሞው የሰበካ አስተዳደር ባስተላለፉት መመሪያ የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር ኮሚቴ በአጥቢያው ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ መመረጡን አውቆ ይህ ምርጫ ከተካሄደበት የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነቱ የተነሳ መሆኑን እና በእጁ የሚገኙ ከማህተም ጀምሮ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኗን ንብረቶች ለአዲሱ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ በጥንቃቄ እንዲያስረክብ በአጽንኦት አሳስበዋል።  በመጨረሻም ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳን የአጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ካህናት እና ምእመናን ከአዲሱ የሰበካ አስተዳደር ኮሚቴ ጋር በመሆን የሰላምን መንገድ ተከትለው፣ መለያየትን አስወግደው፣ በፍቅር እና በአንድነት እንዲያገለግሉ እና እንዲገለገሉ፤ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት አክብረው እንዲያስከብሩ አሳስበዋል።

pic-1የጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በከፊል

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg 0 0 tc https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg tc2014-03-03 06:49:062014-03-03 06:49:06የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ምርጫ አካሄደ
Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የእለተ ሰንበት ቅዳሴ ና ጸሎት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት ከስቶክሆልም ቅድስት ሥላሴ መንበረ ጸባኦት
  • ካህናት
  • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
  • የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ የንግሥ በዓል
  • የአጥቢያው የመተዳደርያ ደንብ ጸድቆ በሥራ ላይ ዋለ
  • ቀዳሚት ሥዑር
  • ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
  • ሆሣዕና
  • የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ
  • +++ የበገና እና የሥነ ጽሑፍ ምሽት +++

በፌስቡክ ያግኙን

© Stockholm Menbere Tsebaot Holy Trinity Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ታሪክ Link to: ታሪክ ታሪክ Link to: አገልግሎት Link to: አገልግሎት አገልግሎት
Scroll to top Scroll to top Scroll to top