ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ

መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው መመሪያ መሠረት ሀ/ስብከቱ ያዘጋጀውን የሠላም እና የእርቅ ጉባኤ ፋይዳ ቢስ በማደረግ በእምቢተኝነታቸው ጸንተው ይባስ ብለው አፍራሽ እንቅስቃሴ ባደረጉ እና እያደረጉ ባሉ የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አስተላለፈ።

የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ በር ያለአግባብ ታሽጎባቸው በአማራጭ ቦታ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት አምልኮተ እግዚአብሔርን እየፈጸሙ ላሉ ምእመናን እና ካህናት በሰጡት ቃለ ምዕዳን በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ከእነርሱ ጋር በተባበሩ ካህናት ላይ የተወሰደው ቀኖናዊ ቅጣት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር እና ተገቢ ባልሆነ ተግባር ላይ የተሳተፉትን ሁሉ ለማስተማር እንደሆነ ገልጸው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነት የሁሉም ድርሻ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሀ/ስብከቱ የተላለፉትን ቀኖናዊ ውሳኔዎች ሙሉ ይዘት ለማንበብ ከዚህ በታች ያሉትን ደብዳቤዎች ይመልከቱ።

ለሰሎሞን በቀለ

ለአባ ወልደሥላሴ

ለቀድሞው የሰበካ አስተዳደር 1

ለቀድሞው የሰበካ አስተዳደር 2

{flike}{plusone}