• እንኳን በደህና መጡ

    በዚህ ድረገጽ . . .

የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን –በዓብይ ኋይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን – አግዐዞ ለዓዳም ሰላም  –እም ይእዜሰ ኮነ –ፍስሃ ወሰላም «ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም፣ ወከመ ኀያል ወኅዳገ ወይን፣ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ = እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው ኀያል ሰውም፣ ጠላቱን በኋላው ገደለ፡፡»       የሚቀጥለው ሊንክ በመጫን ተጨማሪ ፎቶዎችን ይመልከቱ – የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም  

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ መሰረት የሰንበት ት/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ። በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቤተክርስትያኑ አስተዳደሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ፣ የአጥቢያው ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን […]

ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ

መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው […]

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ምርጫ አካሄደ

ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ እና ሥራ አስኪያጁ መጋቤ አእላፍ ተወልደ ገብሩ እንዲሁም የአጥቢያው ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በተገኙበት የካቲት 02 ቀን 2006 ዓ.ም. በ S:t Jacobs Kyrka, […]

ለየካቲት 23 2006 ዓ.ም. (March 2, 2014) በ Vårby skolan ይካሄዳል ተብሎ የተጠራውን ስብሰባ ሀ/ስብከቱ እውቅና የማይሰጠው መሆኑን ገለጸ

እንደሚታወቀው በምእመናን እና በቤተ ክርስቲያኑ የቀድሞ የሰበካ አስተዳደር መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና በአስተዳደሩ በተወሰደው ቤተ ክርስቲያንን የማሸግ ኢ-ቀኖናዊ እርምጃ ላይ መፍትሄ ለመስጠት የሰ/ም/አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ከአንድም ሁለት ጊዜ ወደ ስቶክሆልም መምጣታቸው ይታወሳል። በእነዚህ ሁለት አበይት ስብሰባዎች የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ልዑካን እና ምእመናን በተገኙበት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን እንዲያስረዱ […]

ቋሚ መርሐግብራት

ጸሎተ ኪዳን እና ሥርዓተ ቅዳሴ – እሑድ 06:00 – 12:00

የሰርክ ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት – ማክሰኞ እና ዓርብ 17:30 – 20:00

የሕጻናት የአብነት ትምህርት –  ዓርብ 17:30 – 19:30

የአዳጊዎች መርሐግብር በየ 15 ቀኑ – ቅዳሜ ከ14:00 – 16:30

አገልግሎቱን ይደግፉ

የገንዘብ እገዛ ለማድረግ የሚከተሉትን መረጃዎች ይጠቀሙ።

PlusGiro-konto : 74 35 26-6

International bank No:
SE62 9500 0099 6034 0743 5266

Swift code: NDEASESS

123 252 67 21

ያግኙን

  • Menbere Tsebaot S:T Selassie Etiopiska Ortodoxa Tewahedo Kyrkan i Sverige

  • Org. nr. 802492-9237

  • BOX 496 , 101 29 Stockholm

  • Värmdövägen 622, 13241 SALTSJÖ-BOO

መልዕክት ይላኩልን