በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ
    • ታሪክ
    • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
    • ካህናት
  • አገልግሎት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ህጻናት እና አዳጊዎች
  • ትምህርተ ሃይማኖት
  • ይለግሱ
  • ያግኙን
  • Menu Menu
Blog - Latest News

የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት

የትንሣኤ 2 መዝሙር (ከመጽሐፈ ዚቅ)

ትትፌሣሕ ሰማይ ወትታኃሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይጸውዑ አድባር ወአውግር ወኩሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፡፡

ትርጉም: ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ /ይደሰቱ/ ተራሮችና ኮረብቶችም /ነገሥታት መኳንንት/ ይጩኹ/ይደሰቱ/ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን/ደስታን/ ታደርጋለች።

መልዕክታት

1ቆሮ. 15፥20-41
አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል፡፡ በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአልና፥ በሁለተኛው ሰው ትንሳኤ ሙታን ሆነ፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በክርስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ፡፡

 

1ጴጥ.1፥1-13
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከጴጥሮስ፥ በጳንጦስ፥ በገላትያና በቀጰዶቅያ፥ በእስያና በቢታንያ ሀገሮች ለተበተኑ ስደተኞች፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዳወቃቸው፥ በመንፈስ ቅዱስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ፥ ለተመረጡት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡

ሐዋ.2፥22-37 እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እንደምታውቁት በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእጁ ባደረገው በከሃሊነቱ በተአምራቱና በድንቅ ሥራዎቹ እግዚአብሔር የገለጠላችሁን ሰው የናዝሬቱን ኢየሱስን ስሙ፡፡ እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት፡፡

ምስባክ

ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር
ንዑ ንትፌሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ
ኦ እግዚኦ አድኅንሶ

ትርጉም፦

ይህች እግዚአብሔር የፈጠራት /የሠራት/ ቀን ናት
ፈጽሞ ተድላ ደስታን እናድርግባት
አቤቱ አድነን

ወንጌል ዮሐ.20፥1-19 ከሳምንቱም በመጀመሪያዉ ቀን ማርያም መግደላዊት በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነሥቶ አገኘችው፡፡ ፈጥናም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ጌታተን ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝሙር መጥታ፥ “ጌታዬን ከመቅብር ወስደውታል፤ ወዴትም እንደ ወሰዱት አላውቅም” አለቻቸው፡፡

ቅዳሴ

ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg 0 0 tc https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg tc2014-05-03 19:39:202014-05-03 19:39:20የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት
Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የእለተ ሰንበት ቅዳሴ ና ጸሎት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት ከስቶክሆልም ቅድስት ሥላሴ መንበረ ጸባኦት
  • ካህናት
  • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
  • የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ የንግሥ በዓል
  • የአጥቢያው የመተዳደርያ ደንብ ጸድቆ በሥራ ላይ ዋለ
  • ቀዳሚት ሥዑር
  • ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
  • ሆሣዕና
  • የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ
  • +++ የበገና እና የሥነ ጽሑፍ ምሽት +++

በፌስቡክ ያግኙን

© Stockholm Menbere Tsebaot Holy Trinity Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም Link to: የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን... Link to: በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ Link to: በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top