የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ

አዲስ የሰንበት ትቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት ከደብሩ አስተዳዳሪበኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ መሰረት የሰንበት ት/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ።

በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቤተክርስትያኑ አስተዳደሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ፣ የአጥቢያው ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን ተገኝተዋል።

 

 

 

ጠቅላላ ጉባኤው ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አባላትን በቅዱሳን አበው ስርዓት መሰረት በጸሎት እና በዕጣ የአጥቢያው ሰንበት ት/ቤት ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ መርጧል።

  1. ዳንኤል መኮነን
  2. ምስጋናው ጌታው
  3. ማርያ ፍጹም
  4. ዮሐንስ ገብሩ
  5. ነቢያት ኃይሌ
  6. አዲስ ደርስህ
  7. አማኑኤል በንቲ
  8. ዲ/ን ኪሮስ አብርሃ (የሰበካ ጉባኤ ተወካይ)
በተጠባባቂነት
  1.     ፍሬህይወት ላቀው
  2.     ሰሎሞን ገ/ሥላሴ

በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ ባስተላለፉት መልዕክት “የቤተክርቲያኗን ዶግማ እና ቀኖና ጠብቃችሁ የተጣለባችሁን ታላቅ መንፈሳዊ ኃላፊነት በትጋት ልትወጡ ይገባል።” በማለት በአጽንዖት አሳስበዋል።