በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ
    • ታሪክ
    • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
    • ካህናት
  • አገልግሎት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ህጻናት እና አዳጊዎች
  • ትምህርተ ሃይማኖት
  • ይለግሱ
  • ያግኙን
  • Menu Menu
Blog - Latest News

ገብር ኄር (የዐቢይ ጾም 6ኛ ሳምንት)

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡

ትርጉም: ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡

ምንባባት

2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡ 

1ኛ ጴጥ.5÷1-11 እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ 

የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ “ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።”

ምስባክ

መዝ. 39÷8 “ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡”

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ 

ወንጌል

ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ”

ቅዳሴ

ዘባስልዮስ 

{flike}{plusone} 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg 0 0 tc https://teklehaymanot.se/a/wp-content/uploads/logo-trinity.svg tc2014-03-29 21:11:592014-03-29 21:11:59ገብር ኄር (የዐቢይ ጾም 6ኛ ሳምንት)
Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የእለተ ሰንበት ቅዳሴ ና ጸሎት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት ከስቶክሆልም ቅድስት ሥላሴ መንበረ ጸባኦት
  • ካህናት
  • ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ
  • የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ የንግሥ በዓል
  • የአጥቢያው የመተዳደርያ ደንብ ጸድቆ በሥራ ላይ ዋለ
  • ቀዳሚት ሥዑር
  • ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
  • ሆሣዕና
  • የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ
  • +++ የበገና እና የሥነ ጽሑፍ ምሽት +++

በፌስቡክ ያግኙን

© Stockholm Menbere Tsebaot Holy Trinity Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ደብረ ዘይት Link to: ደብረ ዘይት ደብረ ዘይት Link to: ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት) Link to: ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት) ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት)
Scroll to top Scroll to top Scroll to top